ደጋጋ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት - ከተማዋን ለማሻሻል አብረን እንሰራለን
ደጋጋ ከተማ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ በአልቡኮ ወረዳ አስተዳደር ስር የምትገኝ ስትሆን በ2001 ዓ.ም መዘጋጃ ቤት ተቋቁሞላት ወደ ስራ በመግባት ቀጥሎም የአልቡኮ ወረዳ መቀመጫ በመሆን ለነዋሪወቿ የማህበራዊ የተለያዩ የአስተዳደር ማዕከል ሁና እያገለገለች ትገኛለች፡፡
የከተማዋ የእድገት ፕላን ከአሁን በፊት በ2005 ዓ.ም ተዘጋጅቶ ቢሆንም የፕላን ዘመኑ በመጠናቀቁ ምክኒያት እና የተዘጋጁ ፕላኖችንም ቢሆኑ ወቅቱን ጠብቆ ክለሳ ማድረግ ካልተቻለ በየጊዜው እየጨመረ ከሚሄደው የህዝብ ቁጥር እድገትና ፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ አገልግሎት መስጠት ስለማይቻል የክለሳ ፕላን መስራት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
የደጋጋ ታዳጊ ከተማ ከ10.790° - 10.811° ኬክሮረስና እና ከ39.614° - 39.660° ኬንተሮስ ትገኛለች፡፡ በአነጻሩ የደጋጋ ታዳጊ ከተማ በደቡብ ወሎ ዞን በአልቡኮ ወረዳ ከዞኑ ዋና ከተማ ደሴ በደቡብ በምዕራብ አቅጣጫ የምትገኝ በታዳጊ ማዘጋጃ ደረጃ ያለች ከተማ ናት፡፡
የደጋጋ ከተማ ክለሳ ፕላን ለህዝብ የሚቀርበው በሚቀጥለው ሳምንት ሲሆን ሁሉም ነዋሪዎች እና ባለድርሻ አካላት በማህበረሰብ ስብሰባ ተገኝተው አስተያየት እንዲሰጡ ይጠበቃል...
ይቀጥሉየከተማዋን የመንገድ አውታር ለማሻሻል አዲስ የመንገድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጀምሯል። ይህ ፕሮጀክት የትራንስፖርት ችግር እንዲፈታ ያደርጋል...
ይቀጥሉየከተማዋ መሃከላዊ መኖሪያ ልማት ፕሮጀክት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። አዲሱ የመኖሪያ ልማት ለነዋሪዎች የተሻለ ኑሮ ደረጃ ያቀርባል...
ይቀጥሉደጋጋ ከተማ
አልቡኮ ወረዳ
ደቡብ ወሎ ዞን
አማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ
0997978585
info@degagacity.gov.et