የሳልመኔ ከተማ ማዘጋጃ ጽ/ቤት - አጠቃላይ መረጃ
ስለ ከተማዋ፣ የልማት አቅጣጫዎች እና የአገልግሎት መዋቅሮች ዝርዝር መረጃ
ሳልመኔ ከተማ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ከሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ በአብልኮ ወረዳ አስተዳደር ስር የምትገኝ ስትሆን በ2001 ዓ.ም መዘጋጃ ቤት ተቋቁሞላት ወደ ስራ በመግባት ቀጥሎም የአብልኮ ወረዳ መቀመጫ በመሆን ለነዋሪወቿ የማህበራዊ የተለያዩ የአስተዳደር ማዕከል ሁና እያገለገለች ትገኛለች፡፡
የከተማዋ የእድገት ፕላን ከአሁን በፊት በ2001 ዓ.ም ተዘጋጅቶ ቢሆንም የፕላን ዘመኑ በመጠናቀቁ ምክኒያት እና የተዘጋጁ ፕላኖችንም ቢሆኑ ወቅቱን ጠብቆ ክለሳ ማድረግ ካልተቻለ በየጊዜው እየጨመረ ከሚሄደው የህዝብ ቁጥር እድገትና ፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ አገልግሎት መስጠት ስለማይቻል የክለሳ ፕላን መስራት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
የሳልመኔ ከተማ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ከሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ በአብልኮ ወረዳ አስተዳደር ስር የምትገኝ ስትሆን፡-
በአልቡኮ ወረዳ ውስጥ 10 ወንዞች የሚገኙ ሲሆን እነዚህም፡-
| የወንዙ ስም | ተፋሰስ | ሊያለሙ የሚችሉት መሬት (ሄ/ር) |
|---|---|---|
| ገላና | አዋሽ | 65.5 |
| አባሰደን ተፋሰስ | አዋሽ | 23.59 |
| ሸጠልማጥ | አባይ | 47.25 |
| ሴሱ | አዋሽ | 65.5 |
| በብልኮ | አዋሽ | 25.6 |
በወረዳው አንድ ማይባር የተሰኘ ሀይቅ ይገኛል፡፡ አጠቃላይ 418.25 ሄ/ር መሬት ማልማት ተችሏል፡፡
የመሬት መወሰን፣ መለያ ማድረግ እና ቁጥጥር አገልግሎቶች
የግንባታ ፈቃድ መስጠት እና ቁጥጥር አገልግሎቶች
የንግድ ፈቃድ መስጠት እና እድሳት አገልግሎቶች
መንገድ፣ ውሃ፣ መብራት እና ፖስታ አገልግሎቶች
ትምህርት፣ ጤና እና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች
የገቢ ማሰባሰብ እና አስተዳደር
ሳልመኔ ከተማ መዘጋጃ ቤት ተቋቁሞላት ወደ ስራ በመግባት የአብልኮ ወረዳ መቀመጫ ሆነች፡፡
የከተማዋ የመጀመሪያ የእድገት ፕላን ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ውሏል፡፡
የከተማዋን ሁኔታ የሚያጤን የክለሳ ፕላን ጥናት ተጀምሯል፡፡
የሳልመኔ ከተማ ክለሳ ፕላን (2014-2024 ዓ.ም) ለህዝብ ይቀርባል፡፡
የክለሳ ፕላን ዘመን ያበቃል እና አዲስ ፕላን ይጠናቀቃል፡፡